አገልግሎቶቻችን
የአቡጊዳ የቋንቋ እና የባህል ተቋም ተማሪዎች
አዳዲስ ዜናዎች
የዝግጅቶቻችን ቀን መቁጠሪያ
የቅርብ ጊዜ የዝግጅቶቻችን
የአቡጊዳ የቋንቋ እና የባህል ተቋም
ከእኛ ጋር ይስሩ ፡፡ ከእኛ ጋር ይማሩ ፡፡ ከእኛ ጋር ያሻሽል
እያንዳንዱ ተማሪ ቋንቋውን፣ ባህሉን፣ እና ታሪኩን በሚገባ አውቆ ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፍ ትውልድን መቅረጽ ነው።ተማሪው ከሀገሩ እርቆ እንደመኖሩ መጠን የራሱን ቋንቋ፣ ባህል፣ እና ታሪክ የሚማርበትንዕድል በመፍጠር ለማህበረሰቡ በስፋት ተደራሽ መሆን። በግብረ- ገብ (በመልካም በስነ-ምግባር) የታነጸ ትውልድን መፍጠር። ተቋሙ ከማንኛውም ሃይማኖት/ ከዘር/ እና ከብሔር የጸዳ መሆኑን ማረጋገጥ።ተማሪው በሚኖርበት አካባቢ ካለው ባህል ጋር የራሱን ባህል አዛምዶ (አቀናጅቶ) የሚይዝበትን ስልት መቀየስ እና መርዳት።ተማሪዎች ይበልጥ እርስ በእርስ እየተገናኙ የሚተዋወቁበትን መድረክ መፍጠር።ተማሪዎቹን በጋራ መከባበር እና እርስ በእርስ የመረዳዳት ባህልን በማዳበር ጥሩ ዜጋ እንዲሆኑ መጣር።ተቋሙ ሁል ጊዜም ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለተማሪዎቹ ማቅረቡን መከታተል።የስነ-ምግባር ጉድለት የታየበት ተማሪ በተቋሙ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ቀርቦ ምክር እንዲያገኝ ጥረት ማድረግ።
የአቡጊዳ የቋንቋ እና የባህል ተቋም አባላት
መስታወት ንጉሴ
ዳይሬክተር
የተቋሙ መስራች እንዲሁም ዳይሬክተር* Finance administrator* የወላጆች ኮሚቴ አባል* የቤተመጻህፍት አባል* የባችለር ድግሪ IT ተማሪ* 11 አመት ልምድ
ቃልኪዳን እውነቱ
ረዳት ዳይሬክተር
የ1ኛሀ ክፍል መምህር ከ2018 ጀምሮ በተቋሙ ውስጥ በመምህርነት እየሰራች ያለች።ከተቋሙ ውጪ ልጆችን በማስተማር የ4 አመት ልምድ ያላት ከልጆች ጋር ተግባቢና ልጆችን በጣም የምትወድ።የኮሌጅ ተማሪ
አብሰራ ይሄይስ
አስተዳደር
* የተቋሙ መስራች እንዲሁም አስተዳደር
* Marketing manager
* የዲሲፕሊን ኮሚቴ አባል
* የባችለር ድግሪ ተማሪ
* ልጆችን በማስተማር 7 አመት ልምድ
* የ1ኛ ለ ክፍል መምህር
ደበበ ተክሌ
መምህር.የሥነ ምግባር ኮሚቴ ሃላፊ
የ3ተኛ ክፍል መምህር ከ2019 ጀምሮ በመምህርነት እያገለገለ የሚገኝ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና ባህርዳር ዩኒቨርስቲ በመምህርነት የሰራ።ከልጆች ጋር ማሳለፍና ልጆችን ለማስተማር ከፍተኛ ጥረት የሚያደርግ በተቋሙ ውስጥ የሥነ ምግባር ኮሚቴ ሃላፊ የማስተርስ ዲግሪ ያለው::