የእኛ የሙያ ቡድን አባላት (በከፊል)
መምህራኖቻችን
አስተማሪ ተማሪዎች ዕውቀትን ፣ ብቃትን ወይም በጎነትን እንዲያገኙ የሚረዳ ሰው ነው ፡፡ በአብዛኛዎቹ ሀገሮች መደበኛ የተማሪዎችን ማስተማር አብዛኛውን ጊዜ የሚከፈሉት በተከፈለ ባለሙያ መምህራን ነው ፡፡
የ 3ኛ ክፍል መምህርት
Biruktawit Kiflu
መምህርት
Fasika Yalew
መምህርት
Kalkidan Ewnetu
የግብይት እና የማስታወቂያ ክፍል አስተባባሪ
Mahlete Feleke
የተቋሙ መስራች እና ዳይሬክተር
Mestawet Feleke
መምህርት
Netsanet Feleke
መምህርት
Seble Kelcha
መምህርት
Wubrest Adam
መምህር
Yaphet Teffera
አቡጊዳ የቋንቋ እና የባህል ተቋም የእርስዎ ምርጫ
እያንዳንዱ ተማሪ ቋንቋውን፣ ባህሉን፣ እና ታሪኩን በሚገባ አውቆ ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፍ ትውልድን መቅረጽ ነው።
የኮሚቴዎች ዓላማው
በተቋሙ ውስጥ የተቋቋሙ ኮሚቴዎች
የወላጆች ኮሚቴ
● የወላጆች ኮሚቴ ተቋሙን ለማገዝ በበጎ ፈቃድ በሚያገለግሉ የተማሪዎቻችን ወላጆች በ2018 የተቋቋመ ነው።
● ኮሚቴው በተቋሙ ውስጥ የሚደረጉ ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችና የበአላት ዝግጅቶች በማስተባበር በበላይነት የሚሰራ ነው።
● ለወላጆች ጠቃሚ የሆኑ የውይይት አጀንዳዎችን በማዘጋጀትና የተቋሙን ወላጆች በመጋበዝ ተሳትፎ ያደርጋል።
የወላጆች ኮሚቴ ፕሬዝዳንት
አቶ መላኩ ደሴ
ምክትል ፕሬዝዳንት
አቶ ጸሐይ ሮቢ
እና
የኮሚቴው ጸሐፊ
ወ/ሮ ስመኝሽ መንገሻ

የወላጆች ኮሚቴ
የቤተመጻህፍት ኮሚቴ
ኮሚቴው በ2019 ዓ.ም. በበጎ ፈቃደኛ የተማሪዎች ወላጆች የተቋቋመ ነው። በ2026 ዓ.ም. በተደረገው የመጻሕፍት ቆጠራ መሠረት፣ ቤተ መጻሕፍቱ ከ1,000 በላይ መጻሕፍትን የያዘ ሲሆን፣ ዓላማውም የንባብ ባህልን ማጎልበት፣ ተማሪዎችና ማህበረሰቡ የልጆች መጻሕፍትና የመማሪያ ግብዓቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ ማድረግ እና ቤተሰቦች የቤተ መጻሕፍቱ አባል በመሆን መጻሕፍትን በውሰት በመጠቀም የንባብ ልምዳቸውን እንዲያዳብሩ ማበረታታት ነው።
በተጨማሪም ኮሚቴው በተለያዩ ወቅቶች የተረት፣ የታሪክ እና ሌሎች የባህል ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት የማህበረሰብ ተሳትፎን ለማጠናከር ይሰራል። ወደፊትም ቤተ መጻሕፍቱን በማስፋፋት ለሰፊው ማህበረሰብ ተጠቃሚነት እንዲያደርስ ታቅዷል።
የኮሚቴው ፕሬዝዳንት
አቶ ዮናስ ሮቢ

የዲሲፕሊን/ የስነምግባር ኮሚቴ
1. የዲሲፕሊን ኮሚቴ የተቋቋመበት ዋና አላማ ተቋማችን ከቋንቋ እና ታሪክ ትምህርቶች በተጨማሪ የግብ-ረገብ (የስነ-ምግባር) ትምህርቶችን ይሰጣል። በዚህም የዚህ ኮሚቴ መዋቅር የስነ-ምግባር ጉድለት የታየበትን ተማሪ በግል በማናገር እና በመምከር ተማሪውን ወደ ተሻለ ባህርይ መመለስ ነው።
2. የዲሲፕሊን ኮሚቴው በየክፍሉ ካሉ መምህራን ጋር በመነጋገር ተማሪው ከመምህሩ ጋር ወይም ከክፍል ጓደኞቹ ጋር አለመግባባት ሲፈጥር በዛው ሰአት ወደ ቢሮ ጠርቶ የምክር አገልግሎት በመስጠት ችግሩን ይፈታል። breakout
3. በዲሲፕሊን ኮሚቴው ሁለት ጊዜ የተመከረ ተማሪ ካለበት መጥፎ ባህርይ መመለስ ባይችል ኮሚቴው ለ3ተኛ ጊዜ ለመምከር ወላጅን ይጠራል በወላጅ ፊት ተመክሮ ወላጅም ለማስተካከል ኃላፊነት ይወስዳል። ይህ ባይሆን እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት እንቅፋት የሚፈጥር ከሆነ ለሌሎች ተማሪዎች ደህንነት ሲባል ከተቋሙ ይታገዳል።
4. የዚህ ኮሚቴ ተጠሪ መምህር ደበበ ተክሌ ሲሆን በውስጡ ሦስት አባላትን የያዘ ነው። አባላቱም የተቋሙ ሰራተኞች ናቸው።
• ስለተማሪው የስነምግባር ደንብ በይበልጥ ለመረዳት ገጽ 19 እና 20ን ያንብቡ።
የኮሚቴው ፕሬዝዳንት
መምህር ደበበ ተክሌ

የባህልና ስነጥበባት ኮሚቴ
የዚህ ኮሚቴ ተጠሪ መምህርት ፍቱን ጌታቸው ስትሆን አላማውም ተማሪዎች ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን ያላቸውን ተሰጥኦ እና ችሎታ እንዲያዳብሩ ለማገዝ ነው። ወደ ፕሮግራሙ ለመግባት ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች በየአመቱ የሚወጣውን ማስታወቂያ ተከትሎ ወደ ተቋሙ በመቅረብ የመመዘኛ መስፈርቱን ማሟላት ይኖርባቸዋል። ኮሚቴው በተለያዩ ዘርፎች ላይ ከሚሰሩ ሰዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ተማሪዎችን ባላቸው ችሎታ እና አቅም ለማገዝ የተለያዩ ጥረቶችን ያደርጋል።
የኮሚቴው ፕሬዝዳንት
መምህር ፍቱን ጌታቸው










