ጥያቄዎች

Home / ጥያቄዎች

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች – የቋንቋ ትምህርቶች – አቡጊዳ-የቋንቋ-እና-የባህል-ተቋም

እያንዳንዱ ተማሪ ቋንቋውን፣ ባህሉን፣ እና ታሪኩን በሚገባ አውቆ ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፍ ትውልድን መቅረጽ ነው።ተማሪው ከሀገሩ እርቆ እንደመኖሩ መጠን የራሱን ቋንቋ፣ ባህል፣ እና ታሪክ የሚማርበትንዕድል በመፍጠር ለማህበረሰቡ በስፋት ተደራሽ መሆን። በግብረ- ገብ (በመልካም በስነ-ምግባር) የታነጸ ትውልድን መፍጠር። ተቋሙ ከማንኛውም ሃይማኖት/ ከዘር/ እና ከብሔር የጸዳ መሆኑን ማረጋገጥ።ተማሪው በሚኖርበት አካባቢ ካለው ባህል ጋር የራሱን ባህል አዛምዶ (አቀናጅቶ) የሚይዝበትን ስልት መቀየስ እና መርዳት።ተማሪዎች ይበልጥ እርስ በእርስ እየተገናኙ የሚተዋወቁበትን መድረክ መፍጠር።ተማሪዎቹን በጋራ መከባበር እና እርስ በእርስ የመረዳዳት ባህልን በማዳበር ጥሩ ዜጋ እንዲሆኑ መጣር።ተቋሙ ሁል ጊዜም ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለተማሪዎቹ ማቅረቡን መከታተል።የስነ-ምግባር ጉድለት የታየበት ተማሪ በተቋሙ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ቀርቦ ምክር እንዲያገኝ ጥረት ማድረግ።

የፊደል ገበታ፣ ንባብ፣ የግብ-ረገብ 94%
የታሪክና የባህል ትምህርቶች 91%
ጽሁፍ አጻጻፍ ጨምሮ የንባብ 83%
የኢትዮጲያ የባህላዊ የምግብ አሰራር ፣ የስዕል፣ ውዝዋዜ፣ ተውኔት 95%
0 ተማሪዎች
0 የመማር መርሃግብሮች
0 መምህራን
0 ቅርንጫፎች

ያገኘናቸው ጥያቄዎች? መልሶች አሉን

በየሴሚስተሩ መጨረሻ ላይ በሚኖረው የወላጆችና መምህራን ውይይት (parent and teacher conference) ላይ የቀጣዩ ሴሚስተር ትምህርት ማቴሪያል ሳይላክ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ እና ተማሪው የጀመረውን ሴሚስተር ሳይጨርስ ቢያቋርጥ የቀረውን የሴሚስተር ጊዜ ክፍያ ይከፍላል። ተጨማሪ መረጃ የወላጆች መረጃ ደብተር (parent handbook) ላይ ይመልከቱ።

ትምህርቱ Virginia በሚገኘው ትምህርት ቤታችን መጥተው መማር ለሚፈልጉ እንዲሁም ርቀት ወስኗቸው በአካል መገኘት ለማይችሉም በርቀት (online) ይሰጣል።

ትምህርቱ የሚሰጠው በእድሜና በደረጃ ተከፋፍሎ ስለሆነ ከጀማሪዎች ጀምሮ አራቱም የቋንቋ ክህሎቶች በሁሉም ክፍሎች ይሰጣሉ።

ተማሪዎች የቤት ስራ፣ ፕሮጀክት እና ፈተና ለማስረከብ google classroom ይጠቀማሉ እንዲሁም ተጨማሪ ማቴሪያሎች እና መጽሀፎችን google classroom ላይ ያገኛሉ።

አጠቃላይ የሴሚስተሩ የመማሪያ ማቴሪያል በየሴሚስተሩ መጀመሪያ ላይ ትምህርት ከመጀመሩ አስቀድሞ በፖስታ ይላካል።

የመመዝገቢያ ቅጹን ከሞሉ በኋላ ተማሪው የመግቢያ ፈተና ይወስዳል። ከዚያም ክፍያውን ያጠናቅቃሉ።

ተማሪው የምዝገባ ቅጹን ከሞላ በኋላ የመግቢያ ፈተና ይወስዳል። ፈተናው አራቱንም የቋንቋ ክህሎት ያካትታል። በፈተናው ውጤት መሰረት ከእድሜ እኩዮቹ ጋር በደረጃው ይመደባል።

ፈተናውን ለመውሰድ 3ተኛ ክፍል የሚሰጠውን የጽሁፍ አጻጻፍ ትምህርት/Essay writing/ መማር ይኖርባቸዋል አሊያም በመግቢያ ፈተናው ተመጣጣኝ ውጤት ማምጣት ይኖርባቸዋል።

ከ3 ዓመት – 14 አመት እድሜ ያላቸውን ተማሪዎች እንቀበላለን። ምዝገባ የሚኖረን በየአመቱ የትምህርት መጀመሪያ ላይ ነው ማስታወቂያዎችን ይከታተሉ።

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጋሉ?