ፕሮግራሞቻችን

Home / ፕሮግራሞቻችን

1ኛ “ሀ ”  ክፍል:-ይህ ክፍል እድሜያቸው ከ3-6 አመት የሆኑ ተማሪዎች የፊደል ገበታ፣ ንባብ፣ ግብረ-ገብ፣ እንዲሁም የላሜቦራ የተረት ጊዜን ያካተተ ነው። በተጨማሪም የተለያዩ የእጅ ስራዎችን Art & crafts በክፍልውስጥ ከመምህራኑ ጋር ይሰራሉ።

1ኛ  “ለ ” ክፍል:-በዚህ ክፍል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች እድሜያቸው ከ7-9 አመት የሆናቸው ሲሆን የፊደል ገበታ፣ንባብ፣ የግብ-ረገብ፣ የታሪክና የባህል ትምህርቶች ተካተው ይሰጣሉ።

1ኛ “ሐ”  ክፍል:-ይህ ክፍል እድሜያቸው ከ10- 13 አመት የሆናቸው ተማሪዎች የፊደል ገበታ፣ ንባብ፣ የግብ-ረገብ፣ የታሪክና የባህል ትምህርቶችን የሚማሩበት ነው።

 

 

 

 

በየክፍሉ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች

  • የፊደል ገበታ
  • ንባብ
  • ግብረ-ገብ
  • ላሜ ቦራ

2ኛ ሀ  ክፍል

ይህ ክፍል እድሜያቸው ከ4-7 አመት የሆናቸው ተማሪዎች ፊደላቱን ከነቅጥያዎቻቸው ለይተውየጨረሱ እንዲሁም በንባብ ትምህርት በ1ኛ ክፍል ውስጥ የሚሰጠውን የንባብ ስምንት የደረጃመጻህፍቶችን በሚገባ ያጠናቀቁ ተማሪዎች የጽሁፍ፣ ንባብ፣ የግብረ-ገብ፣ የታሪክና የባህል ትምህርቶችን የሚማሩበት ክፍል ነው።

2ኛ ለ ክፍል

በዚህ ክፍል የሚሰጠው ትምህርት ከ2ኛ ለ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ልዩነቱ በእድሜ መከፋፈሉ ብቻ ነው።

 

 

 

በየክፍሉ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች

  • የጹሑፍ አጻጻፍ
  • ንባብ
  • ግብረ-ገብ
  • የታሪክናየባህል ትምህርት

3ኛ ክፍል

በዚህ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች 2ኛ ክፍል የሚሰጠውን ትምህርት በአጥጋቢ ሁኔታ በመከታተልወደ 3ኛ ክፍል የተዘዋወሩ ወይንም ተቋሙ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና በመውሰድ ውጤታቸው ለዚህ ክፍል የሚያበቃ ውጤት ማምጣት ይኖርባቸዋል። ሁሉም የትምህርት አይነቶች ለየብቻ የሚሰጡበት ክፍል ነው። ጽሁፍ አጻጻፍ (Essay writing) ጨምሮ የንባብ፣ የግብረ-ገብ፣ የባህልና የታሪክ ትምህርቶች ተካተው ይሰጣሉ።

 

 

 

 

በየክፍሉ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች

  • ንባብ
  • የጹሑፍ አጻጻፍ
  • የግብረ-ገብ ትምህርት
  • የታሪክና የባህል ትምህርት

4ኛ ክፍል (“ጽሁፍ ትምህርት”):-ይህ ክፍል በ4ኛ ክፍል የሚሰጠውን የጽሁፍ ትምህርት ለመማር ከ3ተኛ ክፍል ጨርሰው ለመጡ ተማሪዎች የተዘጋጀ ሲሆን በተመጣጣኝ የእውቀት ደረጃ ላይ ያሉ ተማሪዎችንም በመግቢያ ውጤት መስፈርት መሰረት ይቀላቅላል። ይህ የጽሁፍ ትምህርት ለ10 ወራት የሚሰጥ ሲሆን በሶስት ሴሚስተሮች የተከፋፈለ እና በውስጡም ስሁፍ አጻጻፍን፣ ሥነ ቃል፣ እንዲሁም የኢትዮጲያን ታሪክ በጽሁፍ በስፋት የሚያስተምር ክፍል ነው።

4ኛ  ክፍል (“የኢትዮጲያ ታሪክ እና ባህል ትምህርቶች”)ተማሪዎች የኢትዮጲያን ታሪክ እና ባህል በተለያዩ ዝግጅቶች ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ ሲማሩ ቆይተዋል።በተቋሙ በየአመቱ የአድዋ በአል፣ የኢትዮጲያ አዲስ አመት፣ የባህል ቀን፣ የቡሄ በዓል፣ የአጋፔ ዝግጅት እናሌሎችም ይከበራሉ።

4ኛ  ክፍል (ግብረ-ገብ) በዚህ በ4ኛ ክፍል የግብረገብ ትምህርት ራሱን የቻለ አንድ የትምህርት አይነት ሆኖ በየሴሚስተሩ ይሰጣል። ይህ ትምህርት ተማሪዎች በመልካም ስነ ምግባር የታነጹ፣ ሰብዓዊ እሴቶችን ጠንቅቀው የሚረዱ፣ መልካም ባህሎቻቸውን ጠንቅቀው በማወቅ የሚተገብሩ፣ ከማህበረሰቡ ጋር ሰላማዊ ህይወትን የሚያራምዱ፣ ቤተሰቦቻቸውን የሚያከብሩ፣ ኃላፊነታቸውን የሚወጡ ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ እንዲሁምማንነታቸውን ጠንቅቀው በማወቅ በኢትዮጲያዊነታቸው የሚኮሩ ትውልድ እንዲሆኑ የተቀረጸ የትምህርት አይነት ነው።

4ኛ  ክፍል (“ግብረ-ገብ“)ይህ ፕሮግራም የ10 ወር የጊዜ ርዝመት ያለው ሲሆን በውስጡ ሶስት ሴሚስተርን ያካተተ ነው። 3ተኛ ክፍልን በሚገባ አጠናቀው የጨረሱ አሊያም በተቋሙ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና በብቃት የሰሩ መሆን ይገባቸዋል። በዚህ ክፍል የክፍሉን ደረጃ የሚመጥኑ መጻህፍትን በመጠቀም የሚሰጥ ትምህርት ነው።

 

በየክፍሉ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች

  • ጽሁፍ ትምህርት
  • የኢትዮጲያ ታሪክ እና ባህል ትምህርቶች
  • ግብረ-ገብ
  • ንባብ

የበጋ (Summer classes)

ይህ የትምህርት ፕሮግራም ሀምሌ እና ነሐሴ( July -August) የሚሰጥ ሲሆን መደበኛ ትምህርት ሰኔ (June) ከጨረሱ በኋላ ከመደበኛው ትምህርት ውጪ ለሁለት ወር የሚሰጡ አጫጭር ትምህርቶች ናቸው። ከእነዚህም ውስጥ፦

● የኢትዮጲያ የባህላዊ የምግብ አሰራር ● የተለያዩ የእጅ ሙያዎች ● ሙዚቃ/ የሚዚቃ መሳሪያ እና ውዝዋዜ ● የስዕል ትምህርት ● ስነጽሁፍና ተውኔት ● አማርኛ ቋንቋ ለጀማሪዎች የመናገር ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበት /Amharic for beginner speeking only/ እንዲሁም ሌሎችን ትምህርቶች የሚማሩበት ፕሮግራም ነው።

 

 

 

በየክፍሉ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች

  • የኢትዮጲያ የባህላዊ የምግብ አሰራር
  • ሙዚቃ እና ውዝዋዜ
  • ሥነ-ጽሁፍና ተውኔት
  • ሥነ ስዕል

 

ይህ ፕሮግራም ተማሪዎች በመደበኛ ትምህርታቸው ከ7ኛ ክፍል – 12ኛ ክፍል በሚደርሱበት ጊዜ የሚወስዱት የቋንቋ ፈተና ነው። ፕሮግራሙ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት (high school) ቆይታቸው የሚወስዱትን ቋንቋ ትምህርት ፈተናውን ቀድመው በመውሰድ ክሬዲት ማግኘት የሚችሉበትእድልን የያዘ ነው። ተቋማችን የኢትዮጲያዊያን ተማሪዎች በቋንቋቸው እንዲፈተኑ የሚያስችል የአንድ ሴሚስተር ስልጠና ይሰጣል።

 

 

 

 

በየክፍሉ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች

  • ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ የቋንቋ ፈተና

Some Statistics

98%
1ኛ ክፍል ፕሮግራሞች
98%
2ኛ ክፍል ፕሮግራሞች
100%
3ኛ ክፍል ፕሮግራሞች
98%
4ኛ ክፍል ፕሮግራሞች
97%
የበጋ (Summer classes)
98%
የቋንቋ ፈተና