የ 3ኛ ክፍል መምህርት
Biruktawit Kiflu
መምህርት

በዚህ ክፍል በስነ ምግባር ትምህርት ክፍለ ጊዜ መምህሩ ተማሪዎች እንዲረዱ በሚያስችል ሁኔታ በክፍል ውስጥ ውይይት ያደርጋሉ ቀጥሎም የሚሰጧቸውን የስነ ምግባር ምንባብ በማንበብ እና ተያይዞየሚሰጣቸውን ጥያቄዎች በመስራት ሀሳቡን የበለጠ ያጎለብታሉ። በተጨማሪም ከራሳቸው ህይወት ጋር በማያያዝ ለመምህራቸው እና ለክፍል ጓደኞቻቸው ገለጻ ያደርጋሉ።
“ግብረ ገብ” ማለት የመልካም ተግባር፣ የጥሩ ተግባር ወይም የመልካም አድራጎት ትምህርት ነው። ሥነ ምግባር ነው።ይህ ክፍል እድሜያቸው ከ4-7 አመት የሆናቸው ተማሪዎች ፊደላቱን ከነቅጥያዎቻቸው ለይተውየጨረሱ እንዲሁም በንባብ ትምህርት በ1ኛ ክፍል ውስጥ የሚሰጠውን የንባብ ስምንት የደረጃመጻህፍቶችን በሚገባ ያጠናቀቁ ተማሪዎች የጽሁፍ፣ ንባብ፣ የግብረ-ገብ፣ የታሪክና የባህል ትምህርቶችንየሚማሩበት ክፍል ነው።