የተቋሙ መስራች እና ዳይሬክተር
Mestawet Feleke
ዳይሬክተር

ይህ የትምህርት ፕሮግራም ሀምሌ እና ነሐሴ (July -August) የሚሰጥ ለስድስት ሳምንት የሚቆይ ፕሮግራም ነው። የበጋ ትምህርቱ ዓላማ ተማሪዎች ኢትዮጵያዊ ማንነታቸውን እንዲያውቁ የሚያደርግ በማንነት ግንባታ ላይ ያተኮረ ነው። ከትምህርቶቹ በጥቂቱ፡
● የኢትዮጲያ የባህላዊ የምግብ አሰራር
● የተለያዩ የእጅ ሙያዎች ወይም እደ ጥበብ (ጥጥ መፍተል፣ ዳንቴል ስራ፣ የሹራብ ስራ፣ የወረቀት ክራፍት፣ የጸጉር ስራ፣ጥልፍ መጥለፍ፣እና ሌሎችም
● የሙዚቃ መሳሪያ እና ባህላዊ ውዝዋዜ
● ጭቃ እናቡካ
● የስዕል ትምህርት
● ስነጽሁፍና ተውኔት
● አማርኛ ቋንቋ ለጀማሪዎች የመናገር ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበት /Amharic for beginner speaking / እንዲሁም ሌሎች ሀገራዊ ጨዋታዎችን ለምሳሌ፡ገበጣ፣ ቅልልቦሽ፣ ገመድ ዝላይ፣ ሰኞ ማክሰኞ እና ሌሎች ጨዋታዎችና ትምህርቶችን ያካተተ ፕሮግራም ነው።