ይህ ፕሮግራም ተማሪዎች በመደበኛ ትምህርታቸው ከ7ኛ ክፍል – 12ኛ ክፍል በሚደርሱበት ጊዜ የሚወስዱት የቋንቋ ፈተና ነው። ፕሮግራሙ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት (high school) ቆይታቸው የሚወስዱትን ቋንቋ ትምህርት ፈተናውን ቀድመው በመውሰድ ክሬዲት ማግኘት የሚችሉበት እድልን የያዘ ነው። ተቋማችን የኢትዮጲያዊያን ተማሪዎች በቋንቋቸው እንዲፈተኑ የሚያስችል የአንድ ሴሚስተር ስልጠና ይሰጣል።
በሁሉም ፕሮግራሞች ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ በየክፍሉ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና መውሰድ ይኖርባቸዋል።