የተቋሙ መስራች እና ዳይሬክተር
Mestawet Feleke
ዳይሬክተር

ተማሪዎች የኢትዮጲያን ታሪክ እና ባህል በተለያዩ ዝግጅቶች ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ ሲማሩ ቆይተዋል።በተቋሙ በየአመቱ የአድዋ በአል፣ የኢትዮጲያ አዲስ አመት፣ የባህል ቀን፣ የቡሄ በዓል፣ የአጋፔ ዝግጅት እናሌሎችም ይከበራሉ። በእነዚህ ዝግጅቶች ላይ በሁሉም ክፍል ያሉ ተማሪዎች በመሳተፍ የሀገራቸውን ታሪክ እና ባህል ይበልጥ እንዲያውቁ ይደረጋል። በዚህ በሦስተኛ እና አራተኛ ክፍል ግን የኢትዮጲያ ታሪክ እና የባህል ትምህርቶች በጽሁፍ ትምህርት ውስጥ ተካትቶ ይሰጣል። ይህም በውጪው አለም የተወለዱ እንዲሁም በልጅነታቸውም ከሀገራቸው የወጡ ልጆች በማንነት ጥያቄ እንዳይወድቁ፣ የብዙ እሴቶች ባለቤት የሆነችው ሀገራቸው ኢትዮጵያ ያላትን ድንቅ ታሪክ እንዲያውቁ እና በኢትዮጲያዊነታቸው እንዲኮሩ ያስችላቸዋል።ከሚሰጡት ትምህርቶች በጥቂቱ፦ የሀገር ፍቅር፣ ቅርስ፣ ቱሪዝም፣ ባህላዊ ጨዋታዎች፣ እንዲሁም ለተማሪዎች ምሳሌ የሚሆኑ እና የሚያስተምሩ በመልካም ስራ የሚጠቀሱ ኢትዮጲያዊያን ታሪክ በጥቂቱ ተጠቃሾች ናቸው።