የፊደል ገበታ

የፊደል ገበታ
6 students

የፊደል ገበታ

ይህን ትምህርት ለማጠናቀቅ የሚፈጀው ጊዜ በአጠቃላይ 10 ወራት ሲሆን በሶስት ሴሚስተሮች የተከፈለ ነው። የአማርኛ ፊደላት ዲቃላ ፊደላትን (ድርብ የአማርኛ ፊደላትን) ሳይጨምር 231 ናቸው። እነዚህን ፊደላት ለተማሪዎች ቀላል በሆነ እና በአጭር ጊዜ ሊይዙት በሚችሉበት መልኩ በየሴሚስተሩ ተከፋፍለዋል። በዚህም መሰረት በመጀመሪያው ሴሚስተር ባለሁለት እግር 13 ፊደላትን ከነቅጥያዎቻቸው ይማራሉ። በሁለተኛው ሴሚስተር ባለ ሶስት እግር እና እግር አልባ የሆኑ 11 ፊደላትን ከነቅጥያዎቻቸው ይማራሉ። በሶስተኛው ሴሚስተር ባለ አንድ እግር 9 ፊደላትን ከነቅጥያዎቻቸው ይማራሉ። ይህ የማስተማሪያ ዘዴ ላለፉት 3 አመታት ተጠቅመንበት ከፍተኛ የሆነ ጥቅምን እንዳስገኘና ተማሪዎች በቀላሉ ለመለየት እንደቻሉ ተረድተናል። በተጨማሪም በየሴሚስተሩ የተለያዩ አዳዲስ ቃላትን በተለያየ ዘዴ በመስጠት ተማሪዎች የቃላቱን ፍቺ እና አገልግሎት ከመረዳት በተጨማሪ የአማርኛ የቃላት ክምችታቸው እንዲያድግ ጥረት ይደረጋል።

አስተማሪ:

ዳዊት ሙልጌታ
መምህር

ዳዊት ሙልጌታ

የ1ኛ ክፍል ለ መምህር በተቋሙ ውስጥ በመምህርነት እየሰራ ያለ።* የ3 ዓመት ልምድ ያለው ከልጆች ጋር ተግባቢና ልጆችን በጣም የሚወድ።የኮሌጅ ተማሪ
Curriculum is empty
0.0
0 total
5
0
4
0
3
0
2
0
1
0
$149.00

Leave a Reply

Your email address will not be published.