መምህርት
Wubrest Adam
የ2ተኛ ክፍል መምህርት።

ይህ ፕሮግራም የ10 ወር የጊዜ ርዝመት ያለው ሲሆን በውስጡ ሶስት ሴሚስተርን ያካተተ ነው። በዚህ በ3ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች 2ኛ ክፍል የሚሰጠውን ትምህርት በሚገባ ያጠናቀቁ አሊያም በተቋሙ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና በብቃት የሰሩ መሆን ይገባቸዋል። በዚህ ክፍል የሚዳቆን የአንብቦ መረዳት ፍኖት መጽሀፍን መሰረት በማድረግ ሌሎች ተጨማሪ የክፍሉን ደረጃ የሚመጥኑ መጻህፍትን በመጠቀም የሚሰጥ ትምህርት ነው።
በመጀመሪያው ሴሚስተር ምዕራፍ አንድ ዋና ሀሳብ አንድ ታሪክ የተጻፈበት ምክንያት ምን እንደሆነ ስለምን እንደተጻፈ የሚማሩበት። በምዕራፍ ሁለት ደግሞ ገጸ ባህርይ እንዴት መለየትናመረዳት እንደሚችሉ የሚረዱበት ክፍል ነው።
በሁለተኛው ሴሚስተር ምዕራፍ ሶስት መቼትታሪኩ የተከናወነው የት እና መቼ ነው ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚያገኘበት ነው በምዕራፍ አራት ትልም የአንድ ታሪክ መነሻ፣ መካከል እና መጨረሻ ምን እንደሆነ የሚረዱበት ክፍል ነው።
በሶስተኛው ሴሚስተር ምዕራፍ አምስት ምክንያት እና ውጤትለአንድ ነገር መፈጠር ሰበብ የሚሆኑ ነገሮች የሚማሩት ክፍል ነው። በምዕራፍ ስድስት ማነፃፀር በሁለት ወይም ከዛ በላይ በሆኑ ነገሮች መካከል ያለ መመሳሰል እና ልዩነትን ይማራሉ። በእያንዳንዱ ምዕራፍ ላይ ሁለት ሁለት የንባብ መጽሀፍቶችን ይጠቀማሉ።
Leave a Reply